Ethiopian gospel, Mezmur, slow tempo, spiritual worship, clear vocal diction, emotional male vocal, acoustic guitar, atmospheric
5:46
Ethiopian gospel, Mezmur, slow tempo, spiritual worship, clear vocal diction, emotional male vocal, acoustic guitar, atmospheric
5:47
Policy version: pending
Prompt:
### [INTRO] አቤቱ አምላካችን፥ የሰማዩ ጌታ… ኢትዮጵያን ተመልከት፥ ካለህበት ቦታ። የሰማዩ ጌታ፥ የሰማዩ ጌታ… ማረን ይቅር በለን መልሰን በተስፋ...X2 [Verse 1] የአኬልዳማ መሬት፥ ዛሬም ተገዝታለች፤ የንጹሐኑ ደም፥ ምድሪቱን ሞልታለች። የአቤል ደም ከምድር፥ ወደ አንተ ይጮኻል፤ አምላክ ሆይ ተመልከት፥ ፍረድልኝ ይላል። [Silent intimate prayer] አቤቱ፥ ጩኸታችንን ስማ....፤ ጸሎታችንን .... አድምጥ… [Chorus 1] አምላክ ሆይ፥ ኢትዮጵያ፥ ኪዳኗን ይዛለች.....፤ ሁልጊዜም አምላኳን፥ በእምነት ትጣራለች.....። ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያ፥ በፊትህ ወድቃለች....፤ ወደ ቀድሞው ፍቅርህ፥ መልሰን እያለች....።X2 [Verse 2 -] የንጹሐኑ ደም፥ ወደ አንተ ይጮኻል፤ ጆሮህን አዘንብል፥ ስማኝ፥ ፍረድ ይላል። ቅዱሳን አዛውንት፥ በመቅደስህ ወድቀው፤ አንተን ይጠሩሃል፥ ይቅር በለን ብለው። ### [Silent intimate prayer] አቤቱ፥ ጩኸታችንን ስማ....፤ ጸሎታችንን... አድምጥ....... ### [Chorus 2 ] አምላክ ሆይ፥ ኢትዮጵያ፥ ጸሎት ታቀርባለች....፤ ኪዳንህን አስብ፥ ማረን ትልሃለች...። ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያ፥ ምሕረት ጠይቃለች....፤ ዘር እና ሃይማኖት፥ አይለየን እያለች....።X2 ### [Verse 3] እናት በአገሯ ላይ ፥ ይኸው ተዋርዳለች.....፤ ልጆ ቿን ተነጥቃ፥ በደም ተጠምቃለች....። በአደባባይ ወጥታ፥ ለአንተ ትጮኻለች...፤ ልጆችህን አድን ፥ ታደገን እያለች.....፥ ### [Silent intimate prayer] አቤቱ፥ ጩኸታችንን ስማ፤ ጸሎታችንን… አድምጥ...... ### [Chorus ] አምላክ ሆይ፥ ኢትዮጵያ፥ ይኸው ታለቅሳለች.....፤ እርስ--በእርስ አስታርቀን ፥ አንድ አርገን እያለች.....። ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያ፥ አንተን ትጣራለች....፤ ሰላምህን ስጠን፥ ከሰማይ እያለች....። ### [Final Chours repeating] አምላክ ሆይ፥ ኢትዮጵያ፥ ጸሎት ታቀርባለች.....፤ ኪዳንህን አስብ፥ ማረን ትልሃለች....። ኢትዮጵያ፥ ኢትዮጵያ ፥ ምረት ጠይቃለች....፤ ዘር እና ሃይማኖት፥ አይለየን እያለች....።..X2 ### [Softly Spoken Bible Verse] “ኢትዮጵያ እጆቿ ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች ።" ### [Outro - Healing Resolution] እየሱስ…… አንተ ነህ፥ የሕይወት ዋስትና....፤ ለኢትዮጵያ ስጣት፥ ፍቅር እና ጤና....። እየሱስ....... አንተ ነህ፥ የዘላለም ተስፋ....፤ ወደ ቀድሞው ፍቅር፥ መልሰን በተስፋ....። እየሱስ....... አንተ ነህ፥ የኢትዮጵያ ተስፋ፤ ፈውሰን መልሰን፤ አንድ አርገን በተስፋ.... (Repeat Outro 3X) [and ending slow…….]